Posts

ደብተራዎቻችን Vs Psychiatry

Image
Psychiatry ከህክምና ዘርፎች አንዱ ሲሆን ትኩረት አድርጎ የሚሰራው የአእምሮ በሽታዎች ላይ ነው። ይህ የህክምና ዘርፍ ለመፈወስ ከሚሰራባቸው በሽታዎች መካከል፦ የመርሳት ችግር ፣ ከእውነታ ማፈንገጥ ፣ አስከፊ የፀባይ መለዋወጥ እና ከአስተሳሰብ ጋር ተዛማጅ የሆኑ በሽታዎች ተጠቃሽ ናቸው። የምእራቡ አለም ምሁራን ይህን የህክምና አገልግሎት እንደ አንድ ዘርፍ ተቀብለው በዘመናዊ መንገድ መስጠት የጀመሩት ወደ ሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ነበር። በተለይ በጣም አስቸጋሪ ለሆኑ የአእምሮ በሽታዎች መድሃኒት ማግኘት የጀመሩት 21 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ቢሆንም አሁን ድረስ ፈዋሽ መድሃኒት ያላገኙላቸው በሽታዎች አሉ። ወደኛ ስንመለስ ደብተራ (ሊቃውንት) አያቶቻችን የአእምሮ በሽታዎችን መፈወስ የጀመሩት ከአምስት ሺህ ዘመናት በፊት አንስቶ ነው። አያቶቻችን ይህን የአእምሮ በሽታዎችን የመፈወስ ጥበብ ያገኙት ከኖህ አባታቸው ነው። በመፅሐፈ ኩፋሌ ላይ እንደተፃፈው የኖህ ልጆች የአእምሮ በሽታ አጥቅቷቸው ነበር። ኖህም ልጆቹን የሚፈውስበትን ጥበብ በፀሎት ጠየቀ። እግዚአብሔርም መለሰ! መድሃኒት የሚቀምምበትን እና ለዚሁ ህክምና አገልግሎት የሚውሉትን እፅዋትና ማዕድናትን ገለፀለት። ኖህ ያገኘውን ጥበብ በመጠቀም ልጆቹን ፈወሰ። ጥበቡ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሻገር ዘንድ በመፅሐፍ ፅፎ አለፈ። ይህን መፅሐፍ መሰረት አርገው ኢትዮጵያውያን ደብተራዎች መፅሐፍቱን በሁለት መልኩ ከፍለው ፃፏቸው።
 1. የመጀመርያ እፀ ደብዳቤ ይሰኛል።
2. ሁለተኛው እንቁ አእባን ይሰኛል።
 እፀ ደብዳቤ፦ የሰባት መቶዎቹን እፅዋት ዝርዝር ፣ አቀማመማቸው፣ ለምን በሽታ ፈውስ እንደሚሰጡና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን የያዘ ነው።
 እንቁ አእባን፦ እርሱ ደግሞ የማዕድናት ዝርዝሮችን የያዘ ሲሆን ለህክም…

የአየር ጠባይ የሚተነብየው አስደናቂ ተክል

Image
ተፈጥሮ ለመረመራት ሰው አስደናቂ እውነታዎችን ትቸራለች፡፡ ተፈጥሮ እንቆቅልሽ ናት፤ የምትፈልገውም በአድናቆት ስሜት ሆኖ እንቆቅልሹን የሚፈታውን ነው፡፡ አንድ ሰው ተፈጥሮ ውስጥ የበለጠ በዘለቀ ቁጥር የበለጠ እየተደመመ፣ የበለጠ እየተደነቀ ይሄዳል፡፡ በዛሬው የሥነሕይወት አምዳችን፤ ከተፈጥሮ አስገራሚና አስደናቂ ምስጢራት መካከል አንዱን እንመለከታለን፤ የአየር ጠባይ ስለሚተነብየው አስደናቂ ተክል! በሀገርኛ ቋንቋ “የፈረንጅ ጥድ” በመባል ይጠራል፡፡ በሳይንሳዊ አጠራሩ ፒኑስ ኮኒፈር ሲሉት፤ በእንግሊዝኛው ፓይን ይባላል፡፡ ይህ ተክል ከሦስት እስከ ሰማኒያ ሜትር ድረስ የመብቀል አቅም አለው፡፡ በእድሜም ቢሆን አይታማም፤ ከመቶ እስከ አንድ ሺህ ዓመት ድረስ መኖር ይችላል፡፡ በአሜሪካ ሀገር ካሊፎርኒያ ከተማ ውስጥ የሚገኘው እና በቅጽል ስሙ ‹ማቱሳላህ› የተባለው የፈረንጅ ጥድ ዝርያ አራት ሺህ ስድስት መቶ ዓመታት በላይ በመኖር በዓለማችን ከሚገኙ ሕይወት ያላቸው ነገሮች ከቀዳሚው ተርታ ሊመደብ ችሏል፡፡ የፈረንጅ ጥድ አሲዳማ አፈር ላይ እና አሸዋማ አፈር ላይ በምቾት መብቀል ይችላል፡፡ የአየር ጠባይን መተንበይ የሚችለው በምን መንገድ ነው ብለን ስንጠይቅ፤ ስለ ጥዱ ፍሬዎች እናወራለን፡፡ የፈረንጅ ጥድ ፍሬዎች በውስጣቸው የሚገኘውን ዘር ለመበተን አመቺ ወቅትን ይጠብቃሉ፡፡ ይህንንም የሚያደርጉት በአየሩ ውስጥ ያለውን የእርጥበት መጠን በመለካት ነው፡፡ የፈረንጅ ጥድ ደረቅ የአየር ጠባይን ይመርጣል፡፡ የዚህም ምክንያት አየሩ ደረቅ ከሆነ ነፋስ ስለሚኖር በቀላሉ ዘሩ በንፋስ በየአቅጣጫው እንዲበተን ስለሚያደርግ ሲሆን፤ አየሩ እርጥበታማ ከሆነ ግን ዝናብ ስለሚከተል - ዘሮቹንም አጥቦ ስለሚያስቀራቸው - ተመራጭ አይሆንም፡፡ የፈረንጅ ጥድ ፍሬዎች በውስጣቸው የሚገኘውን ዘር ለ…

“ትንሽ ሲቀር…”

Image
ዛሬ አንዲት አጭር ታሪክ ልተርክላችሁ፡፡ ጊዜው አሜሪካ ‘የወርቅ ትኩሳት’ ተብሎ በሚጠራው አባዜ የተለከፈችበት፤ ሁሉም ሰው ወርቅ ለመቆፈር ‘ወርቅ ይገኝበታል’ ወደተባለበት ቦታ ሁሉ የሚጎርፍበት ጊዜ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ የንግዱ ባለሞያው የአቶ ዳርቢ አጎትም ጉዳዩን ሰምቶ ወደ አንድ ተራራ ያመራል፡፡ ብዙ ርዕይ ሰንቋል፡፡ ወርቁን አግኝቶ የሚኖረውን ሀብት እያሠበ በጉጉት እና በአዲስ ጉልበት ወደ ቦታው አመራ፡፡ በቦታውም ደረሰ፤ መቆፈር ጀመረ፡፡
ቆፈረ… ቆፈረ… ከሳምንታት በኋላ… አንዲት ብልጭ የምትል ነገር አየ፡፡ ዓይኑን ማመን አልቻለም፤ የተብለጨለጨው ነገር ወርቅ ኖሯል፡፡ በደስታ እጅጉን ፈነጠዘ፡፡ ይህንን ወርቅ ግን በትንሹ ለመውሰድ አልፈለገም፡፡ ይልቁንም በደንብ እና በስፋት አድርጎ ለመዛቅ እንጂ! ይህንን ለማድረግ ግን አካፋ እና ዶማ ብቻ በቂ አልነበረም… አዲስ እና በብዛት የሚቆፍር ማሽን አስፈለገው፡፡ ይህንን ለመግዛትም ወደ ሜሪላንድ ከተማ ተመለሰ፡፡ በከተማው ውስጥ ለነበሩትም ባለሀብቶች ያገኘውን ነገራቸው፡፡ እነርሱም ተደሰቱ፡፡ ገንዘባቸውንም አሰባስበው እና በብዛት የሚቆፍረውን ማሽን ገዝተው ላኩት፡፡ እርሱም ደግሞ አቶ ዳርቢን ይዞ ወደ ቦታው ተመልሶ መቆፈር ጀመረ፡፡ ቆፈሩ፡፡ ቆፈሩ፡፡ የመጀመሪያው ቁፋሩ ሙሉ ወርቅ ሆነ፡፡ እጅግ ተደሰቱ! በዚህ አካሄድ ምን ያህል ሀብታም እንደሚሆኑ እያሰቡ በደስታ ይሳሳቁ ጀመር፡፡ የተቆፈረው ወርቅ በአጠቃላይ ወደ አንድ ትልቅ ወርቅ አቅላጭ ዘንድ ተላከ፡፡ ከዚያም ደግመው ቁፋሮ ቀጠሉ፡፡
 ቢቆፈር… ቢቆፈር… ቢቆፈር… አንዲት እፍኝ ስንኳ ሊገኝ አልቻለም! በዚህ እጅግ አዘኑ፡፡ ተስፋ ቆረጡ፡፡ ከአሁን በኋላ ወርቅ አናገኝም ብለው፤ ትልቁን መቆፈሪያ ማሽንም ለአንዱ ብረት ገዢ ሸጠውለት ወደ ቀያቸው ተመለሱ፡፡ በዚህ…

‹‹አስተሳሰብህ የትፍ’ታውም ሆነ የእፍፍ’ታው መሠረት ነው!››

Image
ወዳጄ አስተሳሰብህ የትፍ’ታውም ሆነ የእፍፍ’ታው መሠረት ነው! መውጫ በሩ ደግሞ አንደበትህ ነው፡፡ አንደበትህ ጉዳይ አስፈፃሚ እንጂ በራሱ ተናጋሪ አይለም፡፡ አንደበቱን በአስተሳሰቡ የሚገራ እሱ ጀግና ነው፡፡ ነገር ግን አንደበቱ ስሜቱ እንዳዘዘው፣ ደመነፍሱ እንዳጣደፈው የሚናገር ከሆነ ግን አደጋው ብዙ ነው፡፡ ስሜቱን ገርቶ፣ አስተሳሰቡን አብስሎ አንደበቱን የሚያሸንፍ ከውስጡ በሚወጡ ቃላቶች አይደነግጥም፣ አይሸበርም፡፡ ቀድሞውኑ ምን መናገር እንዳለበት ሃሳቡን አብስሎ አንደበቱን ገርቶ ተዘጋጅቷልና፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ በመፅሐፈ ሲራክ ‹‹ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች፤ ትፍም ብትላት ትጠፋለች፡፡ ሁለቱም ከአንድ አፍ ይወጣሉ፡፡›› የሚል ጥልቅ ትርጉም ያለው ቃል እናገኛለን፡፡ ይህ ቃል የሠው ልጅ ሕይወቱን መስራትና መመስረት የሚጀምረው ከውጪው ዓለም ጋር እያነፃፀረ ሳይሆን ከውስጡ ካለው እውነትና እምነት እንደሆነ በሚጥም አገላለፅ ያስረዳናል፡፡ የህይወት ምርጫችን፤ ክፉም ሆነ ደግ ስራችን፤ እውን የሚሆነውና ውሳኔው የሚወጣው ከውስጠ-ሕሊናችን እንደሆነ የሚያሣይ ነው፡፡ አንዲቷን ዕንቁላል ከውጪ ብንሠብራት በውስጡ ያለው ሕይወት ያከትማል፡፡ ከውስጥ ግን ዕንቁላሉ በራሱ ግዜ ቢሠበር ሕይወት ይጀምራል፡፡ ጫጩቶቹም ይፈለፈላሉ፡፡ የዶሮነት ሕይወትም ይጀምራሉ፡፡ ምንም ነገር ከውስጥ ከሆነ ትክክለኛ ሕይወት ይጀመራል፡፡ የዚህ ቃል ቁምነገሩና መልዕክቱ ታላቅ ነው፡፡ ሠው ለሚሠራት ለየትኛዋም ስራው ባለቤቱና ተጠያቂው ራሱ ስለመሆኑ የሚያመላክተን ግሩም ቃል ነው፡፡ ፍምን የዓለም ምሣሌ አድርገንም ልናየው እንችላለን፡፡ ‹‹እፍፍ’ታው ›› እና ‹‹ ትፍ’ታው ›› ደግሞ የሠው ልጅ ለዓለም የሚሠጠው ምላሽና መስተንግዶ ነው፡፡ ፍምን ለማንደድም ሆነ ለማጥፋት ስልጣኑ አስተሳሰባችን መሆኑ…

የአእምሮ ቅኝ ተገዢ የሆነ ሰው ምልክቶች !

Image
በዘመናችን ያልተፈታውና ያልተሰበረው የቅኝ አገዛዝ እስራት የአእምሮ እስራት ነው! ምእራባውያን አፍሪካን በተለይ በሀይል ያልተነበረከከችውን አገራችን ኢትዮጵያን ለማንበርከክ የቀየሱት ስልት አእምሮን ቅኝ መግዛት ነው! ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ኢትዮጵያዊ ንቃተ ህሊናን በምእራባዊ ንቃተ ህሊና ተያያዥ ኮተቶች ለማጨቅ ለዘመናት እጅግ ብዙ ቢሊየን ዶላሮችን አፍሰዋል! እንደ መሳሪያም ፊልም ዘፈን መፅሐፎችን እና መገናኛ ብዙሀኖቻቸውን ተጠቅመውባቸዋል! ለማንኛውም አንድ ሰው አእምሮው ቅኝ ተገዢ ሲሆን የሚያሳያቸው ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው:
_ የራስን ታሪክ መናቅ
 _ የራሱን ጀግኖችና ምሁራና መናቅ
 _ የራሱን ማህበረሰብ ባህላዊ እሴቶች መናቅ
 _ ስለ ራስ ማንነት በኩራት አለመናገር
_ የራስን ቋንቋና ፊደል መናቅ አለመጠቀም
_ የራስን መብት አለመጠየቅና አለማስከበር
 _ ራዕይ አልባ መሆን
_ የሰውነት ቀለም እና ቅርፅን ተጠይፎ አውሮፓዊ ለማድረግ መዳከር
_ በአርቴፊሻል መዋብያዎች ሱስ መለከፍ
 _ እርስ በእርስ መናናቅ
 _ የአገር ፍቅር ስሜት መጉደል
 _ ለማንኛውም የስራ ውጤት የምእራባውያንን እውቅና መዳዳት
_ የራስህ ማንነት ከሌሎች ማንነት በታች እንደሆነ ማመን ከብዙ በጥቂቱ ናቸው! የጎደለውን ከስር መዘርዘር ይችላሉ!

የመናገር ነፃነት ከጥላቻ ንግግር ጋር አልተገናኝቶም ነው! (Freedom of speech is not related to hate speech)

Image
ነፃ ንግግር ማለት የጥላቻ ንግግር ማለት አይደለም፡፡ ነፃነት ሌሎችን መስደቢያ ወይም ማሸማቀቂያ ፍቃድ አይደለም፡፡ ነፃነት ከባድ ኃላፊነት ነው፡፡ ነፃነት ስድነት አይደለም፡፡ ነፃነት ገደብ የሌለው እንዝላልነትም አይደለም፡፡ ነፃነት ገደቡም ሆነ ኃላፊነቱ ሕሊናዊ ነው፡፡ ነፃነትን ባግባቡ ለመጠቀም እውቀት ይፈልጋል፤ ስነምግባር ግድ ይላል፡፡ በነፃነት ስም ሌሎችን የሚያጥላላና ማንነታቸው ላይ የሥድብ ናዳ ማውረድ የነፃነትን እውነተኛ ትርጉም መሳት ነው፡፡ ዘመኑ የዕውቀት ነውና የሃሳብ ልዩነትን በሃሳብ ፍልሚያ ብቻ መታገል የስልጣኔ ምልክት ነው፡፡ እኔ ብቻ ነኝ ልክ፣ እኔ ብቻ አንደኛ፣ እኔ ብቻ ልጠቀም፣ ሌላው የራሱ ጉዳይ የሚል ራስወዳድ አስተሳሰብ ያልበሠለ ሃሳብ ነው፡፡ ብዝሃ ሃሳብን ማክበርና የሌሎችን ማንነት መቀበል የዘመናዊነት ምልክት ነው፡፡ አውሮፓውያን ከጨለማው ዘመን ወደሕዳሴው ዘመን የተሸጋገሩት ለብዝሐ ሃሳብ እውቅና በመስጠት ነው፡፡ ከጥላቻ ምንም እንደማይገኝ በመረዳታቸው ነው አሁን ለደረሱበት ሥልጣኔ ብዝሃ ሃሳብን በነፃነት የሚያንሸራሽሩት፡፡ በሃሳብ ተከራክረው፣ ተጨቃጭቀውና ተፋልመው ተቃቅፈውና ተጨባብጠው የሚለያዩት ሠውየው ላይ ሳይሆን ሃሳቡ ላይ በማተኮራቸው ነው፡፡ ዓለማየሁ ገላጋይ በፍትህ መፅሔት በቁ.20 መጋቢት 2011 ላይ ‹‹የዘመኔ ቅኔ›› በሚል ርዕስ ጥላቻና ፍቅርን እያነፃፀረ ሲናገር እንዲህ ይላል፡- ‹‹ጥላቻ ንፉግ ናት፡፡ ፍቅር ግን ቅርንጫፏ እስኪዘልስ ታፈራለች፡፡ ጥላቻ ራሷ ታስጠማለች፤ ፍቅር ግን ከመርካት ትጀምራለች፡፡ ጥላቻ ፍቅርን አታዳብልም፤ እንኳን ሌላ ራሷን አትወድም፡፡ ለኦሮሞ ብዬ፣ ለትግሬ ብዬ፣ ለአማራ ብዬ፣ ለሶማሌ ብዬ፣ ለሲዳማ ብዬ…… ሌላውን ጠላሁ የሚል ራሱን አይወድም፡፡›› እውነት ነው! ፍቅር የጥላቻ መድሐኒት …

A Soldier’s Story

Image
A story is told about a soldier who was finally coming home after having fought in Vietnam. He called his parents from San Francisco.  “Mom and Dad, I’m coming home, but I’ve a favor to ask. I have a friend I’d like to bring home with me. “Sure,” they replied, “we’d love to meet him.” “There’s something you should know,” the son continued, “he was hurt pretty badly in the fighting. He stepped on a land mind and lost an arm and a leg. He has nowhere else to go, and I want him to come live with us.” “I’m sorry to hear that, son. Maybe we can help him find somewhere to live.” “No, Mom and Dad, I want him to live with us.” “Son,” said the father, “you don’t know what you’re asking. Someone with such a handicap would be a terrible burden on us. We have our own lives to live, and we can’t let something like this interfere with our lives. I think you should just come home and forget about this guy. He’ll find a way to live on his own.” At that point, the son hung up the phone. The parents h…